22ኛውን አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ክልላዊ ማጠቃለያ ፕሮግራም ለማክበር ቅድ መዝግጅት ማድረጉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያክልል የሥነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።
22ኛውን አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን "ትውልድን በስነ-ምግባር፣ ተቋምን በአሰራር'' በሚል መሪ ቃል ክልላዊ ማጠቃለያ ፕሮግራም ለማክበር ቅድ መዝግጅት ማድረጉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።
ታህሳስ 07/2018 ኮሚሽኑ በ22ኛው የአለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን ክልል አቀፍ ማጠቃለያ ፕሮግራም አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፀረ ሙስና ቀን መሪ ቃሉን ከማሰብ በዘለለ፣ ማህበረሰቡ ሙስናና ብልሹ አሰራርን መከላከል እንዲችል ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያስችላል።ሙስና የሀገርን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አውድን የሚያናጋ የሀገርን ህልውና ለአደጋ የሚያጋልጥና ግለሰብን፣ ቤተሰብን፣ ተቋማትን የሚጎዳ አደገኛ ጠላት በመሆኑ በጋራ ለመከላከል ኮሚሽኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።
ሙስናና ብልሹ አሰራር በሀገር ላይ የሚፈጥረው ጉዳት አስቀድሞ ለመከላከል በሥነምግባር የታነፀ ትውልድ መገንባት እንደሚገባ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።ተቋማት ቴክኖሎጂን ተጠቅመው አሰራራቸውን በማዘመን ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለው እና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በዓሉ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
በበዓሉ ሙስና አስመልክቶ ጥናታዊ ጽሁፎች የሚቀርቡ ሲሆን ህብረተሰቡ የሚያስተምሩና የሚያነቃቁ መልዕክቶች እንደሚተላለፉ ጠቁመዋል።የበዓሉ ተሳታፊዎች ወደ ተቋሞቻቸው ሲመለሱ አሰራሮቻቸው መፈተሽና ለቀጣይ ስራ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
በተለይም የሚዲያ ተቋማት በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች በመለየት ለህዝቡ ይፋ በማድረግ ሚናቸው ሊወጡ ይገባል።በአለም ለ22ኛ፣ በሀገራችን ለ21 እንዲሁም በክልላችን ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረው አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በሁሉም ትምህርት ቤቶች እና በየመዋቅሩ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት እና በክልሉ የክላስተር ከተሞች በተለያዩ ሁነቶ እየተከበረ ይገኛል ።
እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ የዘንድሮ የፀረ ሙስና ቀን ክልል አቀፍ ማጠቃለያ በዓል ታህሳስ 9/2018 በወራቤ ከተማ የሚከበር ሲሆን የክልሉ፣ የዞን፣ የልዩ ወረዳና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ ምሁራን፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የወጣቶችና የሴቶች አደረጃጀቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ።