ስለ ኮሚሽኑ
የክልላችንን የኢኮኖሚ ዕድገት በላቀ ደረጃ ለማፋጠን ይቻል ዘንድ የአስፈፃሚ አካላት አደረጃጀት የተልዕኳቸውን ስፋትና ተቀራራቢነት መሰረት ባደረገ መልኩ እንደገና ለመወሰን በፀደቀው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ መንግስት አንቀፅ 55 ንዑስ አንቀፅ 3 በታወጀው መሰረተ በተዘጋጀ የተሻሻለው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 199/2015 ዓ/ም ክፍል 5 ተራ ቁጥር 13(13) መሰረት ተጠሪነቱ ለክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሆኖ እንደተደራጀ ተደንግጓል፡፡ ይህንንም አዋጅ ተከትሎ ሙስናና ብልሹ አሰራር የክልላችንን ብሎም የሀገራችንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን የሚያደናቅፍ ድርጊት በመሆኑ የፀረ-ሙስና ትግሉን የሚያስተባብር ተቋም በሕግ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሃገራችን ብሎም በክልላችን የተጀመረውን የልማት፣ የሠላም እና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ሙስናና ብልሹ አሰራርን መከላከል እንዲሁም መልካም ስነ-ምግባር የተገነባ፣ ሙስናን የሚፀየፍ እና በፅናት የሚታገል ህብረተሰብ በመገንባት የፀረ-ሙስና ትግሉን ማጠናከር እንደሚገባ በመታመኑ በአዋጅ ቁጥር 4/2016 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የስ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሚል ስያሜ ተቋቁሟል::