"ትውልድን በስነ ምግባር ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የዘንድሮው 22ኛው አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን ክልላዊ በዓል አከባበር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በወራቤ ከተማ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከረ ነው።
22ኛው አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን በዓል በክልል ደረጃ በወራቤ ከተማ እየተከበረ ነው።
ወራቤ፣ ታህሳስ 9/2018 (ስልጤ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን)
"ትውልድን በስነ ምግባር ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የዘንድሮው 22ኛው አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀን ክልላዊ በዓል አከባበር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በወራቤ ከተማ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከረ ነው።
በበዓሉ አከባበር ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ባለፉት ጊዜያት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት የሚያሳይ የፎቶ ኢግዚቢሽን ተካሄዶ የእለቱ መርሃ ግብር ጀምሯል።
በሌላም በኩል እለቱን አስመልክቶ በህጻናት የተዘጋጀ የጥበብ ስራ የቀረበ ሲሆን መርሃ ግብሩ በፓናል ውይይትና በሌሎች ዝግጅቶች እንደሚቀጥል ተገልጿል።
በዓሉ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ ለ21ኛ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ እየተከበረ መሆኑም ተመላክቷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ የብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ማሞ ቴጋ፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ዋና ሀላፊና የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ ወ/ሮ ነዒማ ሙኒር፣ የክልሉ አስተባባሪ አካላት፣ የክልል ክላስርተር አስተባባሪዎች፣ የቢሮ ሀላፊዎችና ሌሎች የክልል የዞን፣ የልዩ ወረዳና የወረዳ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።