በስነ-ምግባር የታነጸ አገር ተረካቢ ወጣት ለመገንባት የተቀናጀ ጥረት እንደሚያስፈልግ ተመላከተ፤
በስነ-ምግባር የታነጸ አገር ተረካቢ ወጣት ለመገንባት የተቀናጀ ጥረት እንደሚያስፈልግ ተመላከተ፤
ሆሳዕና ፦የካቲት/2018ዓ.ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ ለመገንባት በትምህርት ተቋማት አካባቢ በቅንጅትና በትብብር መስራት የሚያስችል የግብ ስምምነት ተፈረመ።
የግብ ስምምነቱን የፈረሙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ እና የክልሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ናቸው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ደቼ ፣የግብ ስምምነቱ በስነ ምግባር የታነጸ ብቁና አምራች ዜጋ በትብብር ለመገንባት የሚያስችል ነው።
ስምምነቱ ትብብርና ቅንጅትን የሚያጎለብት ስለመሆኑም ያስረዱት አቶ አሰፋ፣የኮሚሽኑ ተነሳሽነት የሚበረታታ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ማሞ ቴጋ የግብ ስምምነቱ በሆሳዕና ከተማ ሲፈረም ባደረጉት ንግግር፣ስምምነቱ የትውልድ ስነ ምግባር ግንባታ ስራዎችን ከታችኛው መዋቅር ጀምሮ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው።
በቀጣይ በትምህርት ቤቶችና በኮሌጆች አካባቢ ለሚገኙ ክበባት የተለየ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ የተሻለ ግንዛቤ በሀገር ፍቅርና ለሀገሩ ሀላፊነትና ተጠያቂነት የሚወስድ በትውልዱ ውስጥ ለመፍጠር ትኩረት መሰጠቱንም ጠቁመዋል።
ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመሆን በትምህርት ተቋማቱ የስነ ምግባር ትምህርት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚሰሩም ኮሚሽነር ማሞ አስታውቀው፣ ከመምህራንና ከተማሪዎች ጋር በቅርበት ለመስራት መታቀዱንም ጠቁመዋል።
![]() | ![]() |
![]() | ![]() |



