Skip to main content

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት ሁለተኛ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት ሁለተኛ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል።

(ወልቂጤ ፣ሀምሌ 9/2018 ዓ.ም)በመድረኩ የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አፈፃፀም ቀርቦ ተገምግሟል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ተወካይ አቶ ግርማ ጊቻሞ በክልሉ ተቋማትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማዘመን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የተደረገው ጥረት ውጤት እያመጣ ነው ብለዋል።

ኮሚሽኑ 336 ሚሊዮን በላይ የሚገመት ብር በቅድመ መከላከል እንዲሁም ተመዝብሮ የነበረውን የህዝብ እና የመንግስት ሀብት ማዳን መቻሉ አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል።

የስነምግባር ኦፊሰሮችን አቅም በማሳደግ ተጠያቂነት ማስፈን ላይ አሰራሩን ማጠናከር ተገቢ ነው ብለዋው የተቋም አሰራር ወጥነትና ተቀራራቢነት እስታችኛው መዋቅር መጠናከር አለበት ብለዋል።

የሀገር ኢኮኖሚያዊ ሀብት የሚያወድመውን ሙስናን መታገልና ተጠያቂነት ማስፈን ጠንካራ ትግል የሚጠይቅ በመሆኑ አንስተው ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

ከሀብት ምዝገባ አንፃር ለውጥ መኖሩን አንስተው ባላስመዘገቡት ላይ ተጠያቂነት ማስፈን ቀጣይ ተጠናክሮ መሠራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ኮሚሽኑ ሙስናና ብልሹ አሰራር ችግሮች በመፍታት ተጠያቂነትን በማስፈን የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። 

በቢሮው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተጨባጭ ለመቅረፍ አገልግሎቶች እና ተቋማትን ዲጂታል ለማድረግ እየሰራ ያለውን ስራ ማሳደግ እንደሚገባውም ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ የሪፎርም ስራዎችን የማጠናከር ስራውን አጠናክሮ መቀጠል አለበት በማለት የተቋማት የሰው ሀይል ወጥነትን በአሰራርና በጥናት መፍታት እንደሚገባ አመላክተዋል።

በየደረጃው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በማጠናከር ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ውስንነቶች ለመቅረፍ በቅንጅት መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

የክልሉ ስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ ተቋማዊ የሙስናና ብልሹ አሰራርን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችል አሰራር ስርዓት ለመዘርጋት በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ተቋሙ ከመከላከል ባለፈ የሙስና ወንጀል ሲፈፀም ክትትል በማድረግ ለፍትህና ለፖሊስ አካላት የማሳወቅ ስራ እተሰራ መሆኑን ገልፀው የህግ ተጠያቂነት ስራው በሌላ ተቋም የሚፈፀም መሆኑ ውስንነቱን ለማረም በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

 

 
 

 
   
   
Image