Skip to main content

‌‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ተገመገመ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ተገመገመ።

‎(ወልቂጤ፣ ሰኔ 19/2018 ዓ.ም) ‎የክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2019 ዕቅድ ተገምግሟል። የአፈፃፀም ሪፖርትና የዕቅድ ግምገማውን የመሩት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ በበጀት ዓመቱ በኮሚሽኑ የተሻለ ስራ መሰራቱን ጠቁመው የፀረ-ሙስና ትግሉን ሁሉም ዜጋ በጋራ ተረባርቦ ከሰራ ሙስናን መቀነስ ይቻላል ብለዋል። 

‎ኮሚሽነሩ አክለው በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎች ላይ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ጠንካራ ጎኖችን የማስቀጠል ሥራዎች መሰራት እንዳለባቸው አሳስበው በቀጣይ በ2019 በጀት ዓመት ላይ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።

‎በመቀጠልም የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነርና የትምህርትና ስልጠናና አውታሮች ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ኑር ከድር በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎች የኮሚሽኑ አመራሮችና ባለሙያዎች በጋራ በመስራት የተመዘገበ ውጤት አመርቂ መሆኑን ጠቁመው በክልላችን የፀረሙስና ትግሉን ሁሉም ዜጋ በማወቅ እንድከለከል በበጀት ዓመቱ በተለያዩ አመራጮች የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች በስፋት ተሰርተዋል ብለዋል። ይህም በቀጣይ 2019 በጀት ዓመት ላይ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እና ደካማ ጎኖችን በመለየት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ይሰራል ብለዋል።

‎በመቀጠልም የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነርና ሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ፋሲካ ጌታቸው በበጀት ዓመቱ በሙስና መከላከል፣ በሀብት ምዝገባና ማሳወቂያ ስራዎች ላይ የተሻለ ሥራ መሰራቱን ጠቁመው አሁንም ሁሉም የተቋሙ ባለድርሻ አካላት ይህንን ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል መስራት አለባቸው ብለዋል። በቀጣይም በጀት ዓመት ዕቅዱን ወደ ተግባር ለውጦ ውጤታማ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል።

‎የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በኮሚሽኑ የዕ/በ/ዝ/ክ/ግ/ግ/ ዳይ/ ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ሙሉጌታ ታደሠ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተዳርጓል።

‎በሪፖርትና ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማው መድረክ ላይ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮችና ሌሎች የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።
 

 

Image