Skip to main content

በተጠናቀቀው በጀት አመት በክልሉ ከ336 ሚሊዮን በላይ ብር ከብክነት ማዳን ተችሏል-ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ

በተጠናቀቀው በጀት አመት በክልሉ ከ336 ሚሊዮን በላይ ብር ከብክነት ማዳን ተችሏል-ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ

ሀምሌ 21/2018(ወልቂጤ)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ2018 በጀት አመት የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እና የ2019 በጀት አመት መሪ እቅድ የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ ማካሄድ ጀመረ።

የማዕከላዊ ኢትዮዮጵያ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ በመክፈቻ ንግግራቸው በተያዘው በጀት አመት በትምህርት ስልጠናና አወቃቀሮች ማስተባበሪያ ዘርፍ በየደረጃው ያሉ መ/ቤቶች የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ኦፊሰሮች ስልጠና መስጠት ተችሏል። 

በስነ-ምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ላይ ስልጠና ለመስጠት የሚያስችሉ 5 ሞጁሎችን በማሻሻል ለ150 አዲስ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል ኦፊሰሮች የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ተችሏል ብለዋል።

እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ በተጠናቀቀው በጀት አመት ለአንድ ሺህ አንድ መቶ ሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ተችሏል።

ከትምህርት ቤቶች ጀምሮ በየደረጃው በሚገኙ መዋቅሮች ለ2 ሚሊዮን 29, ሺህ 129 የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ እንደተፈጠረላቸው አስረድተዋል።

እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ በ2018 በጀት አመት 336 ሚሊዮን 231 ሺህ 934 ብር ከብክነት ማዳን የተቻለ ሲሆን 2 አምቡላንሶች ጨምሮ 2 ሚሊዮን 613 ሺህ 23 ሄክታር የገጠር መሬትና 25 ሺህ 932 ካሬ ሜትር የከተማ መሬት ማስመለስ ተችሏል።

በመድረኩ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነሮች አቶ ኑሪ ከድር እና አቶ ፋሲካ ጌታቸው ፣ የኮሚሽኑ የማናጅመንት አባላት እና ሠራተኞች፣ የክልል፣ የዞን እና ልዩ ወረዳ የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ተገኝተዋል።
 

 

 


Image