የኮሚሽነር መልዕክት

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥነምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መልዕክት
ኮሚሽነር ማሞ ቴጋ
ሙስና የሀገርን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አውድን የሚያናጋ የሀገርን ህልውና ለአደጋ የሚያጋልጥና ግለሰብን፣ ቤተሰብን፣ ተቋማትን የሚጎዳ አደገኛ ጠላት በመሆኑ በጋራ ለመከላከል ኮሚሽኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።ሙስናና ብልሹ አሰራር በሀገር ላይ የሚፈጥረው ጉዳት አስቀድሞ ለመከላከል በሥነምግባር የታነፀ ትውልድ መገንባት እንደሚገባ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።
ተቋማት ቴክኖሎጂን ተጠቅመው አሰራራቸውን በማዘመን ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለው እና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በዓሉ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል።በበዓሉ ሙስና አስመልክቶ ጥናታዊ ጽሁፎች የሚቀርቡ ሲሆን ህብረተሰቡ የሚያስተምሩና የሚያነቃቁ መልዕክቶች እንደሚተላለፉ ጠቁመዋል።የበዓሉ ተሳታፊዎች ወደ ተቋሞቻቸው ሲመለሱ አሰራሮቻቸው መፈተሽና ለቀጣይ ስራ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።በተለይም የሚዲያ ተቋማት በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች በመለየት ለህዝቡ ይፋ በማድረግ ሚናቸው ሊወጡ ይገባል።በአለም ለ22ኛ፣ በሀገራችን ለ21 እንዲሁም በክልላችን ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረው አለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በሁሉም ትምህርት ቤቶች እና በየመዋቅሩ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት እና በክልሉ የክላስተር ከተሞች በተለያዩ ሁነቶ እየተከበረ ይገኛል ተጨማሪ ያንብቡ
የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች
ዋና ኮሚሽነር |
የስነ-ምግባር ትምህርት ስልጠናና አውታሮች ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ |
የሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል ዘርፍ ኃላፊ |
ኮሚሽኑ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች
|
|
|
የኮሚሽኑ ራዕይ ተልዕኮና አላማ
በ2022 ሙስናና ብልሹ አሰራር ለክልላችን ብልጽግና እንቅፋት እንዳይሆን በማድረግ በአገራችን ካሉት የፀረ-ሙስና ተቋማት ግንባር ቀደም ተቋም ሆኖ ማየት! |
ጠንካራ እና ኃላፊነቱን በብቃት ሊወጣ የሚችል ተቋማዊ አደረጃጀት በመፍጠር፣ ሙስናን ለመከላከል የሚያስችል የሥነምግባር አስተምህሮዎችን በማስተማር፣ በጥናት ላይ የተመሠረተ የቅድመ ሙስና መከላከል ሥራዎችን በመሥራት፣ በህጉ መሠረት የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ሥራዎችን በብቃት በመፈፀም እና ከሌሎች የባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት ውጤታማነትን ማረጋገጥ! |
የመልካም ሥነ-ምግባር ተምሳሌት መሆን፤በጋራ መሥራት፤ለቀጣይ ለውጥ ዝግጁ መሆን፤የተግባር ሰው መሆን፤ |
ዜና






